ማዕከሉ ለ5 ዓመት ሞልቷቸው ለሚሰናበቱ ህፃናት የመሸኛ መርሃ ግብር አካሄደ Dejene Gemechu August 29, 2026

ማዕከሉ ለ5 ዓመት ሞልቷቸው ለሚሰናበቱ ህፃናት የመሸኛ መርሃ ግብር አካሄደ

ማዕከሉ በዚህ ዓመት 5 ዓመት ሞልቷቸው ከማዕከሉ ለሚሰናበቱ ሦስት ህፃናት የመሸኛ መርሃ ግብር አካሄደ። በተጨማሪም ለሁሉም እናቶች የምሳ ግብዣ እና የወላጆች ውይይት ተካሂዷል።
እንደሚታወቀው፣ ማዕከሉ ከ2 ዓመት ጀምሮ ህፃናትን ተቀብሎ እስከ 5 ዓመታቸው ድረስ የመዋዕለ ህፃናትና የህፃናት እንክብካቤ አገልግሎትን በተለይም የህፃናት እንክብካቤ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው እናቶች እየሰጠ ይገኛል።
በዚህ ዓመት 5 ዓመት ሞልቷቸው ከማዕከሉ ለሚሰናበቱት ሦስት ህፃናት የመሸኛ መርሃ ግብር በማዘጋጀት፣ ለሁሉም እናቶች የምሳ ግብዣ እንዲሁም የወላጆች ውይይት ተካሂዷል።
በውይይቱ ወቅት እማሆይ ሥርጉት ሚካኤል ማዕከሉ ለአንድ ወር ዕረፍት ካደረገ በኋላ በመስከረም ወር እንደሚከፈትና አገልግሎቱንም እንደሚቀጥል ለወላጆች አሳውቀዋል።
መርሃ ግብሩ ህፃናቱ ያሳለፉትን ጊዜ በማስታወስ፣ ለቀጣዩ የትምህርት ምዕራፍ መልካም ጅማሬ እንዲኖራቸው መልካም ምኞት የተገለጸበት እንዲሁም በማዕከሉና በወላጆች መካከል ያለውን ትብብር የሚያጠናክር የሚያምር ዝግጅት ሆኖ ተካሂዷል።

The Center held a farewell ceremony for three children who have completed the age of five and are graduating from the Center’s kindergarten program. A luncheon was also organized for all mothers, along with a parents’ discussion session.
As is well known, the Center provides kindergarten and childcare services for children from the age of two until they reach five years of age, particularly supporting mothers who are in need of childcare services.
This year, three children who have reached the age of five were formally farewelled from the Center. The occasion brought together the children, their mothers, and other parents for a luncheon and a meaningful discussion.
During the gathering, Emahooy Srgut Mikael informed the parents that the Center will take a one-month break and will reopen in September, when it will resume its services to the children and their families.
The event provided an opportunity to celebrate the children’s growth and achievements, appreciate the partnership of their mothers and parents, and strengthen the relationship between the Center and the families it serves.

Write a comment
Your email address will not be published. Required fields are marked *